አሸባሪው የሕወሀት ቡድን ሀገር ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ጥሰት በጋራ እና በተባበረ ክንድ ለመመከት ዘብ ሊቆም እንደሚገባ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ ገለጹ

ለህዝብ የማያስብ እና ሀገርን ለማፍረስ እያንሰራራ ያለው የአሸባሪው የህወሀት ዘራፊ ቡድን እያደረገ ያለው ተግባር የሚወገዝ እንደሆነ ነው ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ እንደ ገለጹት አሸባሪው የህወሀት ቡድን መንግስት ለትግራይ ህዝብ በማሰብ ያደረገውን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነቱን በተጻረረ መልኩ እያደረገ ያለው አፍራሽ ተልዕኮ ምን ያህል ቡድኑ ለህዝብ የማያስብ ስለመሆኑ አመላካች ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም አሉ ከንቲባ ጸጋዬ ቱኬ ይህ አሸባሪ ቡድን በተለይም የስልጣን ጥማቱን ለማርካት በማሰብ ህጻናትን ወደ ጦርነት በመማገድ ጭምር እያደረሰ ያለው ኢ-ሰብዓዊ ተግባሩ አለም ሊኮንነው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ከሌሎች የውጭ ሀይሎች ጋር በመቀናጀት ሊያፈርስ እየተጋ የሚገኘው ይህ አሸባሪ ቡድን በተለይም ለግብጽ እና ሱዳን ተላላኪ በመሆን ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ እያደረገ ያለውን ጥረትን አስመለክቶም ከንቲባው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያወግዘው ጠይቀዋል፡፡

የህወሀት አሸባሪ ቡድን ከስምንት ወራት የሞት አፋፍ አፈር ልሶ በመነሳት በተለይም በአጎራባች የአፋር እና የአማሀራ ክልሎች ላይ እያደረሰ ያለው ጥቃት ብዙዎቹን ለከፋ መፈናቀል ከመዳረጉም ባሻገር ለሞት እና አካል መጉደል ዳርጓልም ብለዋል ከንቲባው፡፡

ይህን የዚህን አሸባሪ እኩ ተግባር በመመልከትም መላው የሀገራችን ህዝቦች ከዳር እስከ ዳር በመንቀሳቀስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን እና ለልዩ ሀይላችን ዘብ በመቆም ጭምር አለኝታነቱን ማሳየቱንም ከንቲባው አያይዘው ተናግረዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለም መላው ህዝባችን ለሀገር አለኝታ ለሆነው ደጀን ሰራዊታችን በአይነት እና በገንዘብ እያደረገ ያለው ድጋፍ በተመሳሳይ መልኩ የሚበረታታ እና ይህን አሸባሪ ቡድን የሀገር ነቀርሳ ከመሆን የሚታደገን እንደሚሆን እምነታቸው አንደሆነም ከንቲባው ገልጸዋል፡፡

ለዚህም አሉ ረዳት ፕሮፌሰር ጸጋዬ ቱኬ መንግስት በዛሬው እለት ባወጣው መግለጫ ላለፉት ጥቂት ጊዜያት ያደረገውን የተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነትን በመግታት የማያዳግም እርምጃ በዚህ አሸባሪ ቡድን ላይ ለመውሰድ ተገዷል፡፡

ይህን የመንግስትን አቋም መላው ህዝባችን ከመቀበል ባለፈ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ከዳር የሚያደርሰው እንዲሆንም ከንቲባው ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

የሐ/ከ/አስ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሀሴ 5/12/2013 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post