አጃኢብ ሲዳማ ...! ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እጅን በአፍ የሚያስጭን የድጋፍ ሰልፍ ማካሄድ ጀመረ።

የሲዳማ ህዝብ የህወሓትንና አጋሮቹን የሽብር እንቅስቃሴ የሚያወግዝና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነቱን የሚገልፅ ደማቅና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ማካሄድ ጀመራል፡፡

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ የህወሓትንና አጋሮቹን የሽብር እንቅስቃሴ የሚያወግዝና የሽብር ቡድኑን በማፅዳት ዘመቻው በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ ሁሉም አካላት አለኝታነቱን የሚገልፅ ደማቅና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ከሌሊቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በሐዋሳ ከተማ ዓለም አቀፍ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ባለው በዚህ ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ከክልሉ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳር፣ አቶ ሰለሞን ላሌ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ፣ አቶ አብርሃም ማርሻሎ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን ጨምሮ የክልል፣ የከተማና የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የስራ ኃላፊዎች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ከሁሉም ማህበራዊ መሰረቶች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች በተገኙበት የአጋርነት ሰልፉ በታላቅ ድምቀት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ አካላትም የሽብር ቡድኑን የሚያወግዙ፣ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለክልል ልዩ ሀይሎች እንዲሁም የሽብር ቡድኑን በማፅዳት ዘመቻው ተሳታፊ ለሆኑ ለሁሉም አካላት ባህላዊውን የቄጣላ ስነስርዓትና ትዕይንተ ህዝብ በማካሄድና የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ የሀገርና የወገን አለኝታነታቸውን በተለያየ መንገድ በመግለፅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በድጋፍ ሰልፉ የተሳተፉ የክልሉ ነዋሪዎችም በወያኔ የሚመራው የህወሓት ጁንታ ቡድንና ሸኔን ጨምሮ የሀገር ውስጥና የውጭ ሴረኞችና አሽባሪዎች ሀገር ለማፍረስ የሚያደርጉትን አረመኔያዊ እንቅስቃሴ የህይወት መሰዋዕትነት በመክፈል ጨምር በማክሸፍ ላይ ለሚገኙ አካላት የሚያደርጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም እየገለፁ ይገኛል፡፡

በመላው ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ አሸባሪዎች ይደመሰሳሉ ሀገራችንን አንድነቷ ተጠብቆ ትቀጥላለች ያሉት የሰልፉ ተሳታፊ የክልሉ ህዝቦች ከመከላከል ወደ ማጥቃት ለተሸጋገረው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነቱንና ድጋፉን በነቂስ በመውጣት እየገለፀም ይገኛል፡፡

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሐሴ/14/2013ዓም

ሐዋሳ

Share this Post