03
Oct
2021
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ለመላው የሀገራችን ህዝቦች እንኳን ታሪካዊው የመንግስት ምስረታ ቀን በሰላም አደረሰን ይላል።
ነገ ከጥዋቱ 3:00 ጀምሮ በሀገራችን ታሪክ ህዝባዊ እውቅና የተቸረው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እውን ማድረግን ተከትሎ በህዝብ የተመረጠ መንግስት እውን ይሆናል።
ይህን ልዩ የታሪክ አጋጣሚን አስመልክቶ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በሚሌኒየም አደባባይ ባዘጋጀው ስክሪን የመረሀግብሩን አጠቃላይ ሂደት በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ የሚያቀርብ ይሆናል።
በመሆኑም መላው የከተማችን ነዋሪ ቀኑን የተለያዩ ሀገራት መሪዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ከፍተኛ የውጭ ተቋማት ሀላፊዎች የሚታደሙበትን ይህን የመንግስት ምስረታ እንድትከታተሉ ግብዣውን ያቀርባል።
ኢትዮጵያ በዕለቱ አሸናፊ የምትሆንበትን ይህን ልዩና ታሪካዊ ቀንን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትርን ጨምሮ የአስፈፃሚው አካላት በግልፅ ህዝባዊ አደራን ለሚቀጥሉት 5 አመታት የሚረከቡበት ይሆናል።
ኑ እና አብረን መንግስታችንን እንሹም...የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታ በሚወስነው በዚህ በዓለ ሲመት ላይ አብረን ከፍ እንበል ይላል የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የመን/ኮሙ/ጉዳዮች መምሪያ
መስከረም 23/2014 ዓ.ም
ሐዋሳ