ኪዳነ ምህረት ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን ኪዳነ ምህረት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያዉ የካቶሊክ እምነት ቤተክርስቲያን ሲሆን የተቋቋመዉ በ1956ዓ.ም ነዉ።

ኪዳነ ምህረት ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስትያን

ኪዳነ ምህረት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያዉ የካቶሊክ እምነት ቤተክርስቲያን ሲሆን የተቋቋመዉ በ1956ዓ.ም ነዉ።

ቤተክርስቲያኑ የተመሰረተዉ በወቅቱ በኢትዮዽያ የቫቲካን አምባሳደር በነበሩት አቡነ ሞጆሊ በተባሉ የካቶሊክ እምነት ተከታይ አማካኝነት ነዉ።

ከ1972 ዓ.ም ወዲህ ባሉት ዓመታት ውስጥም አቡነ ዮሰፍ ጋስፓሪኒ የተባሉ ጣሊያናዊ የቤተክርስቲያኑን ህንጻ በአዲስ መልክ በማስገንባት አሁን ያለውን ማራኪ ገፅታ እንዲላበስ አድርገውታል፡፡

የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በተለይ የኮምቦኒ ሚስዮናውያንን ከጣሊያን ሀገር በ1956 ዓ.ም እንዲመጡ በማድረግ በርካታ የልማት ሥራዎችን በከተማው አከናውኗል፡፡

የሚስዮናውያን ማህበሩን የመሰረቱት ቅዱስ ዳንኤል ኮምቦን የተባሉ ጣሊያናዊ ናቸው፡፡ ግለሰቡ በተለይ በምስራቅ አፍሪካ የካቶሊክ እምነትን በማስፋፋት እና የተለያዩ ቅዱስ ተግባራትን በማከናወን የጎላ አስተዋፅዕኦ አበርክተው ያለፉ ናቸው፡፡

የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ለከተማዋ በትምህርት እና በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክታለችል፡፡

የኪዳነ ምህረት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ሐዋሳ ኮምቦኒ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በቤተክርስቲያኗ አማካኝነት የተመሠረቱም ናቸው፡፡

የኮምቦኒ ት/ቤት በሐዋሳ ከተማ የመጀመሪያው መንግስታዊ ያልሆነ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን እነዚህ ተቋማት እስከአሁን ድረስም አገልግሎት እየሠጡ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም በሐዋሳ ከተማ ሎቄ አካባቢ የሚገኘው የቡሹሎ ጤና ጣቢያ በሐዋሳ ከተማ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረ ሲሆን አስከ አሁንም አግልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን በማህበራዊ ዘርፍም የጎላ እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን በከተማዋ የሴቶች ማዕከልን በማቋቋም ሴቶች የትምህር እና የሙያ ክህሎት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፡፡

የሐ/ከ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሐሴ 17/2013

ሐዋሳ

ምንጭ፡- የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ባ/ቱ/ስ/መምሪያ

Share this Post