ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው በመሰየማቸው የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ ገለፁ።

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የፌደሬሽን ምክር ቤትና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የምስረታና የመክፈቻ ጉባኤ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው ተሰይመዋል።

ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች የተውጣጡ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎችም በዛሬው ዕለት በመካሄድ ላይ ያለውን የመንግስት ምስረታና የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድን በዓለ ሲመት በሐዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ በጋራ በመሆን ታድመዋል።

በስድስተኛው የመንግስት ምስረታ የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው በመሰየማቸው የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ታላቅ ደስታ የገለፁ ሲሆን የለውጡ መሪ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሐገራችን የመጣውን ለውጥ እንደሚያስቀጥሉ ያላቸውን ፅኑ እምነትም ጨምረው ገልፀዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም/24/2014ዓም

ሐዋሳ

Share this Post