01
Oct
2021
የተለያዩ ሹመቶችና አዋጆችን በማጽደቅ ነው ጉባኤው የተናቀቀው።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኘሬዝዳንት ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለክልል ም/ቤት የሚመጥኑ አባላት በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቀርበው የህዝብ ይሁንታ ማግኘታቸውን ገልጸው ይህም ትልቅ ሀላፊነት ነው ብለዋል።
ክቡር አቶ ደስታ የም/ቤት አባላት የህዝብ ድምጽ በመሆን የተጣለባቸውን አደራ በአግባቡ ለመወጣት በስራ ሂደት የሚኖሩ ብክነቶችን መቀነስና ወሳኝ በሆኑ በእድገትና የመልካም አስተዳደር አጀንዳ ላይ ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ስራ እንደሚጠበቅ የተናገሩት ኘሬዝዳንቱ ለህዝቡ እንዲሁም ለወጣቱ የሰራ እድል፣ መዝናኛ፣የአቅም ግንባታ፣ በጤናና ትምህርት ትኩረት የሚሰጠው ነው ብለዋል።
የተከበሩ የም/ቤት አባላትም ለክልሉ ህዝብ የሚመለሱ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መኖሩን ገልጸው ለዚህም በቅንነት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በመድረኩ ሲዳማን በወወከል ፌዴሬሽን ም/ቤትን የሚሳተፉ
1.ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ
2.ወ/ሮ ፋንታየ ከበደ
3.አቶ አራርሶ ገረመው እና
4.ወ/ሮ ሀገረፅዮን አበበ መሆናቸው ተገልጿል።
የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መስከረም 20/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ