የህወሀት እና የኦነግ ሸኔን ሀገር የማፍረስ ሴራን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ!!

በሐዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም መላው የሲዳማ ህዝብ አሸባሪዎቹን የህወሀት እና የኦነግ ሸኔን ሀገር የማፍረስ ሴራን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

ከማለዳው 12:00 ጀምሮ የሐዋሳ ከተማን ጨምሮ ከመላው የሲዳማ ክልል የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ተገኝተው በአሸባሪው ቡድን ላይ ያላቸውን ተቋውሞ ገልፀዋል ።

የሰልፉ ተሳታፊዎች ህወሀት ላለፉት 27 ዓመታት ኢትዮጵያን የዘረፈ እና ህዝብን ለመከራና ለስደት የዳረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

እኚህ ሁለት አሸባሪ ሀይሎች ከሌሎች የውጭ ሀይሎች እና የሚዲያ ተቋማት ጋር በመሆን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮን አንግበው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን የገለፁት ሰልፈኞቹ ለዚህም እስከ ግንባር በመዝመት ኢትዮጵያን ለማዳን ቁርጠኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በሰልፉ የሲዳማ ባህላዊ ትውፊት የሆነው "ቄጣላ" እና ሌሎች ትዕይንቶች የታዩ ሲሆን የመላው ሲዳማ ህዝብ ለማንኛውም ሀገራዊ ጥሪ ዝግጁ እንደሆነ፣አንድ በመሆን የሽብር ሀይሉን ማጥፋት እንደሚቻል፣የጁንታው ህልም ቅዠት እንደሚሆን እና የውጭ ሚዲያዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚገልፁ መልዕክቶች ታይተዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት 29/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post