የሎቄ ቤተ-መንግስት

ከሐዋሳ ከተማ ከ6-7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ፊንጫዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ይገኛል የሎቄ በተ-መንግስት፡፡

1951 ዓ.ም እንደተገነባ የሚነገርለት ይህ ቤተመንግስት ለቀዳማዊ ሀይለስላሴ ማረፊያነት ታስቦ የጠቅላይ ግዛቱ እንደራሴ በሆኑትና የንጉስ አንጋፋ ልጅ የሆኑት የልዕለት ተናኝወርቅ ባለቤት ራስ ደስታ ዳምጠው አማካይነት እንደሆነ ይነገራል፡፡

ንጉሱም ወደ አካባቢው በሚመጡበት ጊዜ ከቧለማሎቻቸው ጋር የሚያርፉበት በመሆኑ ለሐዋሳ ከተማ ዕድገት ትልቅ ድርሻ እንዳበረከተ በርካቶች ይስማሙበታል ፡፡

ቤተ-መንግስቱ እንዲገነባ የተመረጠው አካባቢ ከፍታ ቦታ ላይና ከሀይቁ ዳርቻ በመሆኑ የሐዋሳ ከተማ ገጽታን በሙሉ ለመመልከት ያስችላል፡፡

እንዲሁም በክረምትና በበጋ የማይደርቅ ምንጭ ያለበትና መልክ-ዓምድራዊ አቀማመጡም ሳቢና እጅግ ማራኪ ነው፡፡

አጠቃላይ አሰራሩን ስንመለከት የቀድሞ አባቶች የነበራቸውን የኪነ-ህንጻ ጥበብ እንገነዘባለን ቤተ-መንግስቱ የክቡር ዘበኛ ማረፊና የእንግዳ መቀበያ ሲኖሩት የንጉሱ መዋኛ ገንዳ ፤የእጣን ማጨሻና ሌሎችም አገልግሎቶች የሚካሔዱበት ስፍራ ነው፡፡

ምንጭ፡- የሐ/ከ/ባ/ቱ መምሪያ የ2007 ዓ.ም የቱሪስት መመሪያ መጽፍ የተወሰደ

Share this Post