የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዪ ቱኬ ለሲዳማ ክልል ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊና ማኔጅመንት አባላት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን አስጎበኙ።

በጉብኝቱ 4 ዋና ዋና የዳቶ መንገድ ከፈታ ስራ፣ ከሞኖፖል ጥቁር ውሃ ሀገር አቋራጭ መንገድ የ7,5 km የአረንጓዴ ልማት ስራ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ እና የመሐል ከተማ ክ/ከተማ አረንጓዴ ልማት ስራ እንዲሁም በባህል አዳራሽ እና በሀይቅ ዳር ክ/ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ እየለሙ ያሉ የመንገድ ዳር የልማት ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ የተጀመሩ የመንገድ ዳር የልማት ስራዎች እጅግ የሚበረታቱና በሌሎቾም ክ/ከተሞች መስፋት ያለበት መሆኑም ከንቲባው ገልጸዋል።

በታቦር ክ/ከተማ ጥልቴ ቀበሌ ሆጎባ አካባቢ በልማት ተነሺዎች የመንገድ ከፈታ ስራም በማኔጅመንት አባላቱ የተጎበኘ ነው።

የቱላ ዎዬ 4.5 km የአስፓልት መንገድ ስራ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ሲሆን የ3.5 km የድሬኔጅ ስራም በሁለቱም በኩል መሰራቱን መመልከት ተችሏል።

መንገዱ ሁለተኛ ንጣፍ(ልባስ) ላይ የሚገኝ ሲሆን አጠቃላይ አፈጻጸሙም 32% ላይ አንደሚገኝ ተገልጿል።

ለኘሮጀክቱ መዘግየት ተግዳሮት የነበረው የወሰን ማስከበር፣ የመብራት ፖል እና የውሃ መስመር ዝርጋታ ችግሮች ተፈቶ ተግባሩን ማስቀጠልም ተችሏል።

የጉብኝቱ አካል የነበረውና በ10 ሚሊየን ብር የተጠናቀቀው የሐዌላ ቱላ ፖሊስ ጽ/ቤት ህንጻ አገልግሎት መስጠት መጀመሩም የተረጋገጠበት ነው።

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍሰሃ ፍቾላ በጉብኝቱ በርካታ መልካም ስራዎችን መመልከት በመቻላቸው መደሰታቸውን ገልጸው አሁንም ከዚህ በበለጠ ስራዎች እንዲሰሩ ክልሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ህዳር 7/20114

ሐዋሳ

Share this Post