የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በሀዌላ ቱላ ክ/ከተማ እየተካሄዱ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎበኙ።

በዳቶ እና በጫፌ ኮቲ ጃዌሳ ቀበሌ የተከፈቱ መንገዶችም የመሰረተ ልማት ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ነው ከንቲባው የተናገሩት።

በነዚሁ ቀበሌያት በቅርቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉም የመሰረተ ልማት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ።

ከንቲባው በክ/ከተማው ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኝ የመንገድ ከፈታና ጠረጋ መጀመሩን ገልጸው አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት የሚሰራው መሆኑንም አክለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው የመንገድ ከፈታው ስራ እጅግ እንደሚጠቅማቸው ገልጸው መንገዱ በተያዘው አኳኋን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

መስከረም 25/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post