22
Aug
2021
በችግኝ ተከላው ኘሮግራም የተገኙት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰሬ ፀጋዬ ቱኬ በዚህ ዓመት በከተማዋ በርካታ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው የዛሬው ደግም በፓርኩ ሰራተኞች የሚደረግ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ዓለማችን ብሎም ሀገራችን ለሰው ልጆች ምቹ እንድትሆን ችግኝ መትከልና መንከባከብም ያስፈልጋል ነው ያሉት ከንቲባው።
የሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ በበኩላቸው ላለፉት ሁለት ዓመታት በግቢው ውስጥ ከ40 ሺህ በላይ ችግኝች መተከሉን ገልጸዋል።
አቶ ፍጹም የዛሬው ችግኝ ተከላ በሐዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክና በኤፒክ ሰራተኞች መሆኑን ተናግረዋል።
በኘርግራሙ 1000 ችግኞች ለመትከል መዘጋጀቱን የገለጹት ደግም Mr ባሩና ሲሆኑ አረንጓዴን መጠበቅና ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ኘሮግራም መሆኑንም ተናግረዋል።
በኘሮግራሙ መጨረሻ 50 ሺህ የአፍና አፍንጫ መሰፈኛ ማስክ ለከተማ አስተዳደሩ በስጥታ ተበርክቷል፡፡
የሐ/ከ/አሰ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ነሐሴ 15/2013
ሐዋሳ