የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ በሀገራችን ታሪክ በልዩነት የሚታሰበውን የመንግስት ምስረታ ቀንን አስመልክቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ሙሉ ቃል

የመሪነት መርህ መነሻዉ የሀገር ፍቅር ነዉ:: ከሁለት አስርት አመታት በላይ ከኖርንበት የሀገር ፍቅር መኮላሸት የባነንነው ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን የመሪነት በትረ ስልጣኑን ከያዙ በኋላ ነዉ።

እዉነትም ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ የእርሶ ወደ ስልጣን መምጣት ሀገሬ ከገባችበት የመፍረስና የመበታተን አደጋ መታደግ አስችሏል።

የእርሶ መምጣት ደግሞ የኢትዮጵያዊያን እናቶች ጸሎትና እንባ ነዉና ከርሶ ይልቅ የመመረጦ ጥቅም የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ነዉ።

ዛሬም በድጋሚ ኢትዮጵያ እርሶን በጠቅላይ ሚንስትርነት ማግኘቷ ትልቅ እድል ነዉ።

የረገጠችዉ የብልፅግና እርካብ ወደምትፈልገዉ የብልፅግና መንበር ከፍ የሚያደርጋት በመሆኑ ኢትዮጵያዬ ደስ ይበልሽ ለማለት እወዳለሁ።

ዉድ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ በወገናችን ልብ ውስጥ ተዘርቶ የከረመዉ የጥላቻና የመከፋፈል እንክርዳድ መንምኖ ወደ ቃርሚያነት ተቀይሯል፤ ያንን እየለቀሙ ማጥፋት ቀጣይ የኛ የቤት ስራ ይሆናል።

ለዚህም መደላድል ይሆነን ዘንድ ለብልፅግና ፓርቲ በቀጣይ አምስት አመታት ይምራን በማለት ድምጻችሁን መስጠታችሁ የይሁንታችሁ ጉልህ ማሳያ ነዉ።

ብልጽግና ዳግም በውድ ልጇ ላይ በናንተዉ የህዝብ እንደራሴዎችና በአለም ህዝቦች ፊት ከባድ ሀላፊነት ጥላለች።

ምንም እንኳን የተቀበሉት ትልቅ አደራ ቢሆንም ሀገራችንን አሁን ካለችበት በላይ የላቀ ከፍታ ላይ እንደሚያስቀምጧት እምነቴ የፀና ነዉ።

ባለፉት አመታት ብዙ የተበለሻሹ ነገሮችን እያስተካከሉ የመጡ በመሆኑ በቀጣይ አምስት አመታት ለሚኖረን የተሳካ ኢትዮጲያን የማሻገር ጉዞ የተሻለ መደላድል ፈጥረዋል።

በመጨረሻም ለሁላችንም ቀጣዩ ጊዜ ከጠቅላይ ሚንስትራችን፣ ከሚመሩት የብልጽግና መንግስትና የተፎካካሪ ፓርቲ ተሿሚዎች ጋር በመሆን የስኬት ጊዜ እንደሚሆንልን በመረዳት ዶ/ር አብይ አህመድ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎ በራሴና በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስም እመኝሎታለሁ!!!!

ኢትዮጵያውን በአንድነት የሀገራችንን ብልጽግና እናሳካለን::

Share this Post