እንደ ሀገር ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገውን የኮማንድ ስራዎችን ነው የከተማዋ ከንቲባ እንደ ከተማ ተግባራዊ የተደረጉ ስራዎችን የገመገሙት።
ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ ከሀገር መከላከያ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሲዳማ ክልል ልዩ ሀይል፣ የብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የ8ክ/ከተማ አመራሮች እና የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊዎች ጋር በመሆንም ነው የገመገሙት።
እስካሁን በኮማንድ ፖስቱ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች ቢሆኑም ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ከንቲባው ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ በተለይም የከተማዋ ነዋሪዎች የማታ ሮንድንና ቅኝተን በተለያዩ አደረጃጀት በመታገዝ ያከናወነው ተግባር ለከተማዋ ፀጥታ መረጋገጥ በግምገማው ወቅት አበረታች ተደርጎ ተጠቅሷል።
በከተማ ማዕከል የተከናወኑ የኮማንድ ፖስት ስራዎችን በገመገሙበት ወቅትም ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ ከአሉባልታና ከሀሰት መረጃዎች እራሳቸውን በመራቅ እራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅም ተናግረዋል።
ከዚህ ጎን ለጎንም ነዋሪው ከሰላምና ፀጥታ አካላትጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር ከተማውን ከአሸባሪዎች ጥቃት እንዲጠብቅ ከንቲባው አሳስበዋል።
ሕብተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታዎች በሚያገኘበት ወቅት ለጸጥታ ኃይሉ በተቀመጡት የስልክ ቁጥሮች በመስጠት የአሸባሪውን ቡድን ተልዕኮ ማምከን እንደሚጠበቅ ከንቲባው ገልጸዋል።
የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ በበኩላቸው ሀገራችን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ በንቃት እንዲጠብቁ ተናግረዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 4/2014 ዓም
ሐዋሳ