የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቶኪዮ 2020ኦሎምፒክ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘታችንን አስመልክቶ ለመላው የሀገራችን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

"እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ!!"

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በቶኪዮ 2020ኦሎምፒክ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘታችንን አስመልክቶ ለመላው የሀገራችን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በብዙ ፈተናዎች መሀል ድልን ማጣጣም በጣም ደስ ያሰኛል! ያሉት ከንቲባው በተለይ ድሉ ሀገራዊ ሲሆን ደግሞ ለተቀሩት ስራዎቻችን በድል መጠናቀቅ ማሳያ እና ተስፋን የሚያሰንቅ በመሆኑ ስሜቱ ይለያል ሲሉ ይገልፃሉ።

አትሌት ሰለሞን ባረጋ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በአለም አደባባይ ከፍ ያደሰገው ሲሆን ኢትዮጵያ ዛሬ በቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ በ10,000ሜትር ሩጫ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች!! ለዚህም ድል እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁም ነው ያሉት ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ።

የዛሬው ድል እንደሀገር የገጠሙንን ፈተናዎች በስኬት እንደምንወጣ ማሳያ በመሆኑ በድጋሚ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ደስታቸውን ለመላው የሀገራችን ህዝቦችና ለከተማው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

Share this Post