የሚመለከታቸው የፍትህ አካላትና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት በተካሄደው የውይይት መድረክ የመምሪያው የ2014 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ሰነድ የቀረበ ሲሆን ሰፊ ውይይትም ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም ጥራት ያለውና ተገልጋይ ተኮር አገልግሎት በመስጠት እንደከተማ ፍትህን ከማረጋገጥ ረገድ በጥንካሬና በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን አንስተው በስፋት ተወያይተዋል።
ፍትህን በማስፈን የወንጀል ድርጊትን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ረገድ እንዲሁም የህፃናትን ሴቶችን ጥቃት ከመከላከል ረገድ የሶስትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር እና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና ህግና አሰራርን የሚከተል ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባም የመድረኩ ተሳታፊዎች ጠቀመዋል።
መድረኩ በ2013 በጀት ዓመት የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጉድለቶችን በመለየትና በማረም ህዝባችንን በቅንነት ለማገልገል ያለመ ነው ያሉት አቶ አበጀ አስረሳኸኝ የሐዋሳ ከተማ ዐቃቤ ህግ መምሪያ ኃላፊ በአመለከከትና በክህሎት የዳበረ ተልዕኮ እና ተግባር በአግባቡ የሚፈፅም ባለሞያ በማፍራት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ከማሳደግ ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱን ነው በመድረኩ የገለፁት።
ጉድለቶችን በማረም እና ፈጣን፣ጥራት ያለውና የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን እንገኛለን ያሉት ኃላፊው በፍትህ አካላትና በባለድርሻ አካላት ቅንጅት እና የጋራ ጥረት የሐዋሳ ከተማን ዕድገት የሚመጥን የህግ ስርዓት ለመትከል በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
ከዚህ አኳያ የተለያዩ የህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችን በመጠቀም በመሰረታዊና በወቅታዊ የህግ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ተገልጋዩ ህብረተሰብ መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝም የመምሪያው ኃላፊ አቶ አበጀ አመላክተዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
መስከረም/13/2014ዓም
ሐዋሳ