21
Dec
2021
በከተማዋ የ5 ወራት የገቢ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
መድረኩን የመሩት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እና የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅ/ ጽ ሀላፊ አቶ ታምሩ ተፈሪ ናቸው።
ከንቲባው በመድረኩ ባስተላለፉት መልእክት የአመራር አካላት ህብረተሰቡን በንቃት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ሁሉም ሰው በተሰማራበት ዘርፍ የተሰጠውን ሀላፊነት በብቃት መወጣት አለበት ያሉት ከንቲባው የቀጣይ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ አሁን ካለው የተሻለ እንዲሆን ይጠበቃል ብለዋል።
የገቢ አፈጻጸሙ ጥሩ የሚባል ቢሆንም ከዚህ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል።
እንደ ከተማ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ በጥብቅ ድስፒሊን የሚመራ መሆኑን ከንቲባው ገልጸው ይህም ተገቢው ክትትል የሚደረግበት መሆኑን አሳውቀዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ታህሳስ 11/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ