የቅድመ ካንሰር ምርመራን ማድረግ የሴቶችን ጤንነት ከማስጠበቅ አኳያ የጎላ ፋይዳ እንዳለው የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት ሴት ተመራጮች ኮከስ አባላት ገለጹ።

ይህ የተገለጸው የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት 2ኛ ዙር ሴት ተመራጮች ለኮከስ አባላት በተዘጋጀ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ነው።

የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ካሰች ተፈራ ሴት የም/ቤት አባላት በዘርፉ ግንዛቤ ይዘው እስከ ቀበሌ በመውረድ ማስተማር እንድችሉ ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል።

ክብርት ወ/ሮ ካሰች እናቶች የቅድመ ካንሰር ምርመራን እንዲያደርጉ ቤት ለቤት በመሄድ ጭምር ለማስተማር ቁርጠኛ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

ካንሰር በሴቶች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳትና የህይወት ማጥፋት ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ የሚገባ ነው ሲሉ ክብርት ወ/ሮ ካሰች ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሰጡት የሐዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ባለሙያ የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት እሳቱ ናቸው።

ወ/ሮ ትዕግስት የማህጸን ጫፍ ክንሰር እና የጡት ካንሰርን የበሽታውን አስከፊነትና ገዳይ መሆኑን በተመለከተ ዘርዘር ያለ ገለጻ አቅርበዋል።

ችግሩ አሳሳቢ ቢሆንም በሴቶች ዘንድ ግንዛቤው እንዲሰፋ ከማድረግ አኳያ ግን ሰፊ ክፍተት መኖሩንም ገልጸዋል።

ከተከበሩ የም/ቤት አባላት መካከል አብዛኛዎቹ እንደገለጹት በርካታ እናቶች በካንሰር ምክንያት እንደሚሞቱ ተናግረዋል።

በተለይም ሳይንሳዊ ህክምናን በማቆም ወደ ባህላዊ ህክምና ብቻ የሚያደሉ ሴቱች ላይም ጉዳቱ የከፋ መሆኑን አክለዋል።

በመሆኑም ያገኙትን ግንዛቤ ለማስተላለፍና የሴቶችን ህይወት ለመታደግ እንደሚሰሩም በመድረኩ ቃል ገብተዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ታህሳስ 26/ 2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post