የትራፊክ ህግና ደንብን በማክበር አደጋን እንቀንስ!

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ልማት መምሪያ።

መምሪያው የ2013 ዓ/አፈጻጸም እና የ2014 ዓ/ም እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በመድረኩ የክልሉ እና የሐዋሳ ከተማ የስራ ሀላፊዎች፣ ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረት የተውጣጡ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

"አዲስ ህይወት በአዲስ ተስፋ" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የንቅናቄ መድረክ በዋናነት ዓላማው የትራፊክ አደጋን መቀነስ ማስቻል ነው።

የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋን የሚመጥን የትራንስፖርት ስርዓትና የመንገድ ልማት ስራ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት፣ ጉዳትና ንብረት መውደም ምክንያት የሆነውን የትራፊክ አደጋ አሽከርካሪዎች፣ እግረኞችም የተቀመጡ ህጎችን መተግበር እንዳለባቸው ገልጸው የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃትም ትኩረት የሚሻ ነው ብለዋል።

በ2014 ዓ/ም ከተማዋ በዘርፉ የሰለጠነ የትራፊክና የመንገድ ልማት ስራን እንድታከናውን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ብለዋል።

የሐዋሳ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አዳነ አየለ በበኩላቸው መድረኩ በ2013 ዓ/ም የተስተዋሉ ክፍተቶች በ2014 እንዳይደገሙ የምንማርበት ይሆናል ብለዋል።

አቶ አዳነ አክለውም የትራፊክ አደጋ ገዳይ ከሚባሉ በሽታዎች ባልተናነስ የሰው ህይወት እየቀጠፈ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉ በዘርፉ በቂ ክህሎትና ግንዛቤ ይዘው ሌሎችን ማሳወቅ ይጠበቃል ያሉት ሀላፊው ችግሩን ለመቀነስ ተቀናጅቶ መስራትን ይጠይቃል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ከከተማዋ ዕድገት ጋር ተያይዞ ሀገር አቋራጭ መንገድ ላይ አደጋው እንደሚበዛ የተገለጸ ሲሆን ሞተር ሳይክል፣ ጋሪዎች፣ ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው።

ህብረተሰቡም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ተብሏል።

ህብረተሰቡ የሚያደርገው ጥንቃቄ እንዲዳብርና በዘርፉ ያለው ግንዛቤ እንዲጎለብት የተጠናከረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ት/ት ሊሰጥ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ታህሳስ 12/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post