የትራፊክ አደጋን በጋራ መቀነስ የሚያስችል ንቅናቄ ተካሄደ

መነሻው ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር እስከ ፒያሳ በተደረገ የእግር ጉዞ ነው የ2014ዓ/ም የትራፊክ አደጋን መቀነስ ንቅናቄ የተደረገው።

በማስጀመሪያ ኘሮግራሙ ላይ የተገኙት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ሐዋሳ ከተማ በትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።

የሰው ህይወትና ንብረት እየወደመ ባለው በዚህ ዘርፍ ተግዳሮቱን ለመቀነስ በአሽከርካሪና በእግረኛ ዙሪያ የወጡ ህጎችንና ደንብን ማክበር ያስፈልጋል ብለዋል።

የተሽከርካሪ የቴክኒክ ብቃትን በተገቢው ማረጋገጥ እንደሚገባ የተናገሩት ከንቲባው የዘርፉ ባለሙያዎችም ጉዳቱን ለመቀነስ ሀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ነው ያሉት።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር መንገድና ትራንስፖርት ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ አዳነ አየለ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ መቀነስ የሚቻለው ህብረተሰቡን ማሳተፍ ሲቻል ነው ብለዋል።

አቶ አዳነ አክለውም እየበዛ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ህብረተሰቡን ለማነቃነቅና ባለድርሻ አካላትም ሚናቸውን እንዲወጡ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ታህሳስ 11/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post