የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ!!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በጠየቀው መሰረት የፍትህ ሚኒስትሩ ዶ.ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አሁን በሰጡት መግለጫ በ48ሰዓት ውስጥ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚፀድቅ ረቂቅ አዋጁን በዝርዝር ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

እንደ ፍትህ ሚኒስትሩ ገለፃ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የማስፈፀምና የመገምገም ሀላፊነትን የገለፁ ሲሆን:-

የክልል እና የፌደራል ሰራዊትን የማዘዝ፣ዕድሜው የደረሰን ወጣት ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ የማድረግ፣ የሰዓት ዕላፊ ገደብ የመጣል፣የመገናኛ ዘዴዎች እንዲዘጉ የማድረግ፣በሽብር የተጠረጠረን አካል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በህግ ጥላ ስር የማዋል፣በሽብር የተጠረጠረ አከባቢን ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መበርበር፣ የፀጥታ ችግር ባለበት አከባቢ የከባቢውን መዋቅር በከፊልም ሆነ በሙሉ ማገድ እና በርካታ ስልጣኖች ያሉት መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

የተከለከሉ ጉዳዮች

1ኛ:- የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ዕዙን እንቅስቃሴ የሚገታ ነገር ማድረግ

2ተኛ:- ለሽብር አካል ድጋፍ ማድረግ

3ተኛ:- የአደባባይ ስብሰባ ሰልፍ ያለፈቃድ ማድረግ

4ተኛ:- ከፀጥታ አካላት ዕውቅና ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ

5ተኛ:- መታወቂያ፣ፓስፖርት አለመያዝ ከሌላቸው ከአከባቢያቸው ተመዝግበው ጊዜያዊ መታወቂያ ማግኘት

6ተኛ:- ወሳኝ የምርትና አገልግሎት ስራን ማስተጓጎል

7ተኛ:- ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አለአግባብ ዜጎችን ማንገላታት እና በመምሪያው የወጣውን አዋጅ መጣስ

የሚሉ አንኳር አዋጆች ሲሆኑ ነገር ግን ሊሻሻል የሚች እና ዝርዝር መመሪያ የሚወጣለት መሆኑን ገልፀዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post