የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ

ይህ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄደው የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ አባልና እጩ የከተማ ከንቲባዎች በተገኙበት በውቢቷ ሐዋሳ ከተማ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ እና የትብብር መድረኩ ፕሬዝዳንት፣ ዶ/ር መስፍን አሰፋ የኢፌድሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የከተማ ልማትና የቤቶች ዘርፍ ሚንስትር ዲኤታ፣ አቶ ካሊድ አብድራህማን በኢፌድሪ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታን እንዲሁም አቶ አንዷለም ጤናው የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ከንቲባዎች በተገኙበት መድረኩ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ሐምሌ/28/2013/ዓም

ሐዋሳ

Share this Post