በሐዋሳ ከተማ ግብርና መምሪያ የአለም አቀፍ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀንን ምክንያት በማድረግ ለባሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ።
በመድረኩ በፀረ ሙስናና በስርዓተ ጾታ ዙሪያም ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በዓለም አቀፍ ለ34ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን "አገልግሎትን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግና ስርጭቱን መግታት" በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሐዋሳ ከተማ ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባየሁ ላሊማ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከራሳችን የሚፈለገውን ጥንቃቄ እያደረግን ቤተሰቦቻችንን እና በአቅራቢያችን የሚገኙትን ሁሉ ማስገንዘብ ስንችል ነው ብለዋል።
አቶ አበባየሁ አክለውም ሙስና ለሀገር እድገትና ልማት ጸር መሆኑን ተናግረው ይህንን እኩይ ተግባር መፀየፍና መጥላት ከያንዳንዳችን ይጠይቃል ብለዋል።
በስርዓተ ጾታ ላይ ያለንን የተዛባ አመለካከት በማስተካከል ዜጎች ለሀገር እድገት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተግዳሮቶችን ማስወገድ ተገቢ ነውም ብለዋል አቶ አበባየሁ።
በመደረኩ ተገኝተው በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ የህይወት ተሞክሯቸውን ያስተላለፉት ወ/ሮ ዘነበች ቲሮ ከ22 ዓመት በፊት የነበረውን የበሽታውን አስከፊነት በማንሳት አስተማሪ መልእክት አስተላልፈዋል።
በተሰጠው ግንዛቤ ማስጨበጫ አሁንም የቫይረሱ ስርጭት መኖሩ የተገለጸ ሲሆን እያንዳንዱ ወላጅ ከቤተሰብ አባሉ ጋር ግልጽ ውይይት ማድረግና ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 21/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ