የከተማዋን እድገት የሚመጥን ጥራት ያለውና የተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ረ/ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገለፁ።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለልጣን ከክልል የጤና ጉዳዮች ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በ(JSC) የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2014 ዓም የጋራ ዕቅድ የዝግጅት መድረክ በሐዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው ከተሞች በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ እንደሚገኙ የገለፁት የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣውን የተሻለ የጤና አግልግሎት ፍላጎት የሚመጥን ጥራት ያለውና የተሻለ አገልግሎት ተደራሽነት ማረጋገጥ ወቅቱ የሚጠይቀው ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነም አመላክተዋል።

ክቡር ከንቲባው አያይዘውም እንደ ከተማ በዘርፉ የሚታየውን የአገልግሎት ፍላጎት የሚመጥን ጥራት ያለውና የተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመው ወቅቱ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት ለማዘመን የድጋፍ፣ የክትትልና የቁጥጥር ስራውን በጋራና በተቀናጀ መንገድ ከማስኬድ ረገድ የመድረኩ ሚና የጎላ እንደሆነም ገልፀዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሐሴ/20/2013ዓም

ሐዋሳ

Share this Post