መደበኛ ጊዜ ኖሯቸው በከተማዋ ተግባራዊ እየሆኑ ያሉት የፅዳት ዘመቻዎች የሐዋሳ ከተማን ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ምቹ እንደሚያደርጋት ይታመናል።
በዚህም ረገድ ህብረተሰቡ አካባቢውን ከማፅዳት ጀሞሮ እንደ ከተማ በዘመቻ መልክ በየጊዜው የሚደረጉ የፅዳት ስራዎች አበረታች ለውጦች እያስመዘገቡ ይገኛል።
የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ዛሬ በከተማዋ ከማለዳው ጀምሮ የተደረጉ መደበኛ የፅዳት ዘመቻዎችን ከካቢኒያቸው ጋር በመሆን አፅድተዋል።
በዚህ ወቅት ከንቲባው እንደገለፁት የፅዳት ዘመቻዎቹ የሐዋሳን ውበት ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረጉ ረገድ ትልቅ እገዛ እያበረከቱ ይገኛሉ ብለዋል።
በቀጠይም ህብረተሰቡ ወጥነት ያለው ተሳትፎ በማድረግ ሐዋሳን ለዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች በማብቃት ረገድ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ከንቲባው የገለፁት።
የሐዋሳ ከተማ የብልፅግና ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ካሱ አሩሳ በበኩላቸው በየጊዜው የሚደረጉ የፅዳት ዘመቻዎች የከተማዋን ህብረተሰብ ጤና ከመጠበቅ ባሻገር ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ተመራጭ ከተማ እያደረጋት ይገኛል ብለዋል።
ስለሆነም መላው የከተማዋ ነዋሪ በተለያዩ አደረጃጀቶች በመታገዝ በዘመቻው ከምንጊዜውም በላይ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ነው አቶ ካሱ ያስረዱት።
በዘመቻው በሴፍትኔት ፕሮግራም ታቅፈው ተሳትፎ እያደረጉ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል በዘመቻ ላይ ያነጋገርናቸው እንደገለፁት ሐዋሳ በሀገራችን ከሚገኙ ከተሞች ፅዱና ውብ መዳረሻ እንደሆነች ተናግረዋል።
ይህን የከተማዋን ገፅታ ይበልጥ ለማጎልበትም ህብረተሰቡ በየሳምንቱ አካባቢውን በማፅዳት እያደረገ ያለውን ተሳትፎን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ጠይቀዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 4/3/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ