የካይዘን ስራ አመራር ፍልስፍና እና የቢኤስሲ ትግበራን በአግባቡ መተግበር ውጤታማ እንደሚያደርግ ተገለጸ።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሰራተኞች የቢኤስሲ እና የካይዘን ስልጠና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆኑም ታውቋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አበባየሁ ላሊማ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ከስልጠናው የሚገኘውን እውቀት ወደ ግብርናው ዘርፍ በማምጣት ከልማዳዊ አሰራር መውጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

ለውጡን ለመቀበል መዘጋጀትና መለወጥም ያስፈልጋል ያሉት አቶ አበባየሁ ስልጠናው እንደግል ህይወትም ሆነ እንደተቋም እውቀት የምንጨምርበት እና አንድ ለውጥ የምናስመዘግብበት ሆኖ አሰራሮችን በማሳለጥ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ጥቅምት 4/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post