የድል ዜና

የጋሸና ግንባር በወገን ጦር ቁጥጥር ስር ሆነ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው “ዘመቻ ለህብረብሄራዊ አንድነት” በድል መገስገሱን ቀጥሏል።

በዘመቻ ለህብረብሄራዊ አንድነት በጋሸና ግንባር የአርቢት፣ የአቀት፣ የዳቦ እና የጋሸና ከተሞችን ከጠላት ጦር ሙሉ ለሙሉ በማስለቀቅ በወገን ጦር ስር ለማድረግ ተችሏል።

የሀገር ህልውናን ለመታደግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የወገን ጦር በሁሉም ግንባሮች ወደ ከፍተኛ ማጥቃት በመግባት ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ይገኛል።

ለወገን ብርታትን፣ ለቀጣይ ድሎች ማስፈንጠሪያ የሚሆን፣ ለህዝብ ደግሞ ሀሴት የሚፈጥር፤ በአንፃሩ ለጠላት የማይጠገን ስብራት የሆነ የድል ዜና ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተሰጥቷል።

ዘገባው፦ የኢ ቢ ሲ ነው።

Share this Post