ግብጽ በመርዛማ ጊንጦች ተመታች

በግብጽ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተተፈጠረ የጎርፍ ማዕበል በአገሪቷ ደቡባዊ አቅጣጫ ትልቋ ከተማ የሀነችው አስዋን አካባቢ ያሉ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ወድመዋል።

ነዋሪዎችም መርዛማና ገዳይ በሆኑ ጊንጦች ተወረው ከ500 በላይ ሰዎች መነደፋቸው ተገልጿል።

በዚሁ ጎርፍ አማካኝነት ከበረሃ ጉድጓዶች መውጣታቸው የተነገረላቸውና መርዛማና ገዳይ ናቸው የተባሉ ጊንጦች ከጎርፍ አደጋው ወደተረፉ መኖሪያ ቤቶች በመግባት ሰዎችን ተናድፈዋል።

አራት ኢንች፣ ስድስት ጥንድ ዐይኖች እና በጭራቸው ሙሉ ገዳይ መርዝ የተሸከሙ ተናዳፊ ጊንጦች አርብ ሌሊት ብቻ 503 ሰዎችን መንደፋቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አረጋግጠዋል።

በአካባቢው የሚገኙ ሆስፒታሎችም በጊንጥ በተነደፉ ሰዎች መጨናነቁን የገለጸው የኒዮርክ ታይምስ ዘገባ፤ የጤና ባለሙያዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ሳይቀር የጥንቃቄ መልዕክትና የህክምና አማራጮችን እያስተላለፉ መሆናቸው ተገልጿል።

በጊንጥ የተነደፉት ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን፤ የህክምና ተቋማትም የመድሀኒትና መሰል አቅርቦቶችን ለማሳደግ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በሀይማኖት ከበደ

አካባቢህን ጠብቅ‼

ወደ ግንባር ዝመት‼

ሠራዊቱን ደግፍ‼

ምንጭ፦ ኢ ፕ ድ

Share this Post