ዘንድሮ ለ16ኛ ጊዜ የሚከበረው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን አስመልክቶም ነው የታቦር ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በዓሉን ያከበሩር።
በዚህ ክብረ በዓል ላይ የሐዋሣ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት ም/አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ካሰች ተፈራ የዘንድሮውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ሀገራችን ለህልውናዋ ዘመቻ እያደረገች ባለችበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
በዚህም አሉ አፈ ጉባኤዋ ህዝቡ በወንድማማችነትን እና ህብረት በመታገዝ የሀገሪቱን ልኡላዊነት ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በላቀ መልኩ ዘብ መቆም ያስፈልጋል ብለዋል።
በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የታቦር ክ/ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ፍቅሬ በበኩላቸው የህልውናውን ዘመቻ አስመልክቶ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ግንባር መዝመት በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ መነሳሳት ፈጥሯል ብለዋል።
ሀገሪቷ ከህወሀት ወራሪ ሀይል ነፃ እስክትወጣ ድረስ ህብረተሰቡ በግንባር ያለውን ደጀን በማገዝ የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ነው አስተዳዳሪው የገለፁት።
በፕሮግራሙ በዓሉን አስመልክቶ የብሔር ብሔረሰቦችን አንድነትን የሚገልጽ ጽሁፍ ወርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በተሣታፊዎችም የጥያቄና መልስ ውድድር ተደርጓል።
የፕሮግራሙ ተሣታፊዎች የኢትዮጵያን ሉአላዊነትና ዳር ድንበር ለማስከበር ሲል የማይተካ ህይወቱን እየሰዋ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል።
የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ
ህዳር 22/2013 ዓ.ም
ሐዋሳ