ነገ ማለዳ የማይለወጥ ቀጠሮ እንያዝ አሉ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ

ከንቲባ ፀጋዬ ቱኬ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው 'የፍቅር መዲና በሆነችዉ ሐዋሳ በአንድነትና በልማት ደምቀን ለክለባችን በጋራ እንሩጥ' በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ለዚህም ነገ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ መላው የስፖርቱ ቤተሰብ ለሐዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ድጋፍ በአንድነት ለመሮጥ እንዲነሳ ጭምር በመልዕክታቸው ከንቲባው ጠቁመዋል።

ቀኑ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባሻገር የልማት፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የልምላሜና የብልፅግና ተምሳሌት በሆነችዉ ሐዋሳ የአዲስ ዘመን የመልካም ምኞት ብስራት በማድረግም ህብረተሰቡ ተሳትፎውን እንዲያደርግ ጭምር ነው በመልዕክታቸው ያስተላለፉት።

Share this Post