ነገ ከተሽከርካሪ ነፃ ሆነው የሚውሉ መንገዶች በሐዋሳ

ከሱሙዳ እስከ ማዘጋጃ ቤት አደባባይ ድረስ ያለው መንገድ ነገ ከተሽከርካሪ ፍሰት ነፃ ሆነው የሚውሉ መንገዶች መሆናቸውን የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

መንገዶቹ ከጥዋቱ 12:00 እስከ ምሽት 12:00 ድረስ በሐዋሳ ከተማ ከተሽከርካሪ ነፃ ሆነው ስለለመቆየታቸውም ነው መምሪያው ያስታወቀው።

በዚህም መሰረት ነገ በ12/102014 ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ከሱሙዳ አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት አደባባይ እና በሴንትራል ሆቴል አድርጎ እስከ አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አደባባይ ድረስ ያለው መንገድ ከማንኛውም ተሽከርካሪ ነፃ ሆኖ የሚቆይ ይሆናል ሲልም ነው መምሪያው የገለፀው።

በእነዚህ መንገዶችም በዋናነት እግረኛና የብስክሌት ተጠቃሚዎች ብቻ የሚገለገሉ መሆኑን የገለፀው መምሪያው ተሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ በሆኑ መንገዶች እንዲጠቀሙ በማለት አሳስቧል።

እንደ መምሪያው ሀላፊ ይህ አይነቱ እርምጃ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል፣ በካይ የተሽከርካሪ ጭስ ለመቀነስ፣ የእግር እንቅስቃሴ ለማበረታታት፣ ለትራንስፖርት የሚወጣ ወጪ ለመቀነሰ እና ብስክሌት ጋላቢዎችን ለማነቃቃት ስለመሆኑ ተገልጿል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ሰኔ11/2014ዓ.ም

ሐዋሳ

Share this Post