የሐዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የከተማ ማዕከል የመንግስት ሠራተኞች የ2016 ዓ ም የ2ተኛ ሩብ አመት መሠረታዊ ድርጅት የአባላት ኮንፈራንስ አካሄደ።

በኮንፍረንሱ ላይ የሀዋሳ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ታጁዲን እንድሪስ እና የፖርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ተመሰገን ጴጥሮስ ለአባላቱ ተገኝተዋል።

በኮንፍረንሱ የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት አባላትና አመራሮች ያለፉት 6ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ኮንፈረንስ እና በቀሪ ስድስት ወራት የተከለሰ ዕቅድ ዙሪያ ዉይይት አካሂዷል።

በመድረኩ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች የተነሱ ሲሆን በተለይም በመደበኛ ስብሰባዎች፣በፓርቲ ተልዕኮ አፈፃፀም እና በልማት ስራዎች ተሳትፎ በጠንካራ አፈፃጸም የተነሱ ሲሆን በቀጣይ ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተነስተው ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።

በመድረኩ ፊት የወጡ ህዋሳት ተጠናክረው መቀጠል እንዲችሉ የእውቅናና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

Share this Post