04
Sep
2022
የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪ
ነሐሴ 29/2014 ዓ/ም
ሐዋሳ
መነሻውን ሐዋሳ ስሙዳ በማድረግ በተጀመረው የሩጫ ውድድር ላይ የሲዳማ ክልል፣ የሐዋሳ ከተማ የስራ ሀላፊዎች፣ አርቲስቶችና የስፖርት ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
የሩጫ ውድድሩን በስፍራው ተገኝተው ያስጀመሩት የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ኘ ፀጋዬ ቱኬ ከተማዋ ለቱሪዝም፣ ለእንቨስትመንትና ለኑሮ ምቹ መሆኗን ገልጸው የሐዋሳን ከነማ ክለብ ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።
ለክለቡ ውጤታማነት በጋራ እንሰራ ሲሉም ነው ከንቲባው የተናገሩት።
የሐዋሳ ከነማ ደጋፊዎች ማህበር ኘሬዝዳንት አቶ ባዩ በልጉዳ ክለቡ ከ6 ዓመት በኋላ የሩጫ ውድድር ማዘጋጀቱን ገልጸዋል።
አቶ ባዩ ከለቡ በ1996 ዓ/ም እና በ1999 ዓ/ም ሻሚፒዮን እንደነበረ አስታውሰው አሁን ላይ ከ10 ዓመት በኋላ ወደ አራተኛ ደረጃ መምጣቱን አክለዋል።
በቀጣይ ዓመትም ክለቡ ሻምፒዮን ለመሆን የሚያዳግተው ነገር እንደማይኖር ገልጸው
የደጋፊ ማህበሩ ዋና ዓላማም ክለቡን ህዝባዊ ማድረግ ነውም ሲሉ አክለዋል።
በህጻናት፣ በታዳጊዎችና በአዋቂዎች በተደረገው የሩጫ ውድድር ከ1ኛ እስከ 10ኛ ለወጡት የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።