የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የ9 ወራት አፈጻጸሙን በመገምገም በቀሪ 3 ወራት የሚያከናውናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መከረ

መምሪያው በዚህ በበጀት አመቱ የ9 ወራት አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት በአዲስና በነባር ፍቃድ እድሳት እንዲሁም ያለ ንግድ ፍቃድ የሚከናወኑ የንግድ ስራዎችን ከመከላከል አንፃር የላቀ ውጤት ማስመዝገቡ ተመላክቷል።

የመምሪያው ሀላፊ ወ/ሪት በላይነሽ ገዳ በመድረኩ በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ህጋዊ አሰራርን ተከትለው እንዲሰማሩ ከማድረግ አንፃር ለውጦች መኖራቸውን ገልፀዋል።

በዚህ ረገድ በተለይም በህገ ወጥ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦች ላይ የሚደረጉ የዋጋ ጭማሬዎችንም አስመልክቶ መምሪያው ባደረገው ክትትል ጠንከር ያለ እርምጃ መወሰዱንም ነው ኃላፊዋ ያስረዱት።

ከመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ምርት እጥረት ጋር ተያይዞ ችግር መኖሩን የገለፁት ሀላፊዋ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተለየ ቅንጅታዊ ስራ ካልተሰራ የሚፈለገው ለውጥ ለማምጣት እንደማይቻልም አያይዘው አስረድተዋል።

ይህ ሆኖ ግን በቀጣይ 3 ወራት በከተማዋ የሚታየውን ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለማስቀረትና ገበያውን ለማረጋጋት ህጋዊነት የሌላቸው የንግድ እንቅስቃሴዎችን ከመቆጣጠር አንፃር መምሪያው በትኩረት እንደሚሠራ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በግምገማ መድረኩ የተገኙ ባለ ድርሻ አካላት በተለይም ከየጎዳና ንግድ ፣ ከነዳጅ፣ ከፍጆታ እቃ ዋጋ ጫማሪ ጋር ተያይዞ ሊታረሙ የሚገባቸው አሰራሮች እንዳሉ ጠቁመዋል።

በተያያዘም ባለ ድርሻ አካላቱ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንፃርም የሚስተዋሉ ችግሮችን በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ዙሪያ መምሪያው ቅንጅታዊ አሰራሩን ማዘመን እንዳለበትም ተናግረዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ሚያዝያ 5/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post