Sidaamu Dagoomi Qoqqowi Mootimma Hawaasi quchumi gashshooti rosu biddishshi 2014M.D rosu millimillo battala hananfi. በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2014 ዓ/ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ተጀመረ።

Sidaamu Dagoomi Qoqqowi Mootimma Hawaasi quchumi gashshooti rosu biddishshi 2014M.D rosu millimillo battala hananfi.

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2014 ዓ/ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ተጀመረ።

በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ ክልላዊ መንግስት በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የ2014 ዓ/ም የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

በመድረኩ የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ሀላፊ አቶ ታፈሰ ገ/ማሪያም፣የሐዋሳ ከተማ አመራሮች፣መምህራን፣ ሱፐርቫይዘሮች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረ/ኘሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ለትምህርት ዘርፍ ትኩረት የሰጡ የአለም ሀገራት የተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸው እንደሀገራችን ብሎም እንደ ሐዋሳ ከተማ በ2014 ዓ/ም ለዘርፉ የምንሰጠው ትኩረት የላቀ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በከተማዋ በ2013 ዓ/ም በዘርፉ የተጀመሩ በርካታ ስራዎች መኖሩን የገለጹት ከንቲባው በበጀት ዓመቱ ፈታኝ ከነበረው ኮሮና በሽታ ጋር የተያያዘ ተግዳሮትን በብቃት ለተወጡ መምህራን ምስጋና አቅርበዋል።

ከንቲባ ፀጋዬ ለተሻለ የትምህርት ጥራት መምህራን የራሳቸውን እውቀት ማጎልበት እንደሚኖርባቸው መልእክት አስተላልፈው የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍም እንደማይለይ ነው የገለጹት።

አጀንዳው ትኩረት የሚሰጠው በመሆኑ የተማሪዎችን ችግር እየለየን የተሻለ ት/ት ለመስጠት በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ከንቲባ ፀጋዬ።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ደስታ ዳንኤል በ2013 ዓ/ም ኮሮና በሽታ ካሳደረው ጫና በመነሳት ለ2014 የት/ት ዘመን መከላከያዎቹን ከመጠበቅ ጎን ለግን የተጀመሩ የመማሪያ ክፍሎችን የማጠናቀቅ፣ ውሃ ለሌላቸው ት/ት ቤቶች የውሃ መስመር ማስገባት እና ተጨማሪ ወንበሮችን ለማሰራት በበጀት መደገፉን ገልጸዋል።

አቶ ደስታ ኮሮናን እየተከላከልን በ2014 ዓ/ም የተሻለ ትምህርት መስጠት እንዲቻልም ተጨማሪ ክፍሎችን የማሰራት፣ ተማሪዎች በወረቀት በተዘጋጅና በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት እንዲያገኙም ጥረት ይደረጋል ብለዋል።

ለዚህም የወላጅች እገዛ የጎላ መሆኑን ነው አቶ ደስታ የተናገሩት።

በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በክፍል ውስጥ የመመር ማስተማር ስራ ላይ ልዩ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን ያከሉት አቶ ደስታ ትምህርት ቤቶች ከወላጆች ጋር የሚኖራቸው ውይይትም ይቀጥላል ብለዋል።

በመድረኩ በቀረበ ሰነድ ውይይት የተደረገ ሲሆን የተነሱ ሀሳብና አስተያየት እንደ ግብዓት የሚያገለግሉ መሆኑ ከመድረክ ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊ አካላት የትምህርት ዘርፍ

ተግዳሮቶችን ማስወገድ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት የሁላችንንም ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

በተለይም ከኮሮና በሽታ ጋር በተያያየዘ ላለ ዘርፈ ብዙ ችግር ተጋግዘን የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በጋራ አንሰራለን ብለዋል።

የሐ/ከ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ነሐሴ 12/ 2013 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post