የሐዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2014 ዓ.ም 2ኛ ዙር የቀበሌ ም/ቤት አፈጉ-ባኤዎች የምክክርና የዘጠኝ ወራት አፈፃፀሙን የገመገመበት መድረክ አካሄደ

የሐዋሳ ከተማ ምክር ቤት 2014 ዓ.ም 2ኛ ዙር የቀበሌ ም/ቤት አፈጉ-ባኤዎች የምክክርና የዘጠኝ ወራት አፈፃፀሙን የገመገመበት መድረክ አካሄደ

የሐዋሳ ከተማ ም/ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ደምሴ ዳንጊሶ በመድረኩ የቀበሌ ምክር ቤቶች የሕዝብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ለዚህም የቀበሌ አፈ ጉባኤዎች የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው የቀበሌ ምክር ቤቶች ተሞክሯቸውን በመወሰድ እና ወደ ራሳቸው በማስፋት የሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባም ነው አፈ ጉባኤው ያስረዱት።

በመድረኩ የቀበሌ ምክር ቤቶች የ2014 ዓ.ም የ9 ወራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይትም ተደርጓል።

በቀረበው አፈፃፀም ላይም እንደ ከተማ የህዝብ ተሳትፎ በማረጋገጥ፣ መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ የግልፅነትና ተጠያቂነት አሰራር እንዲጎለብት የየደረጃው ምክር ቤት አባላት ያላቸውን ድርሻ ማመላከት ተችሏል።

በቀረበው አፈፃፀም ላይ ሀሳባቸውን የሰጡት ተሳታፊዎቹ ህግ አውጪው አካል ከህግ አስፈፃሚው ጋር በመቀናጀት ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደርን እንደ ከተማ እውን ለማድረግ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የሐ/ከ/አስ/የመ/ኮ/ጉ/መምሪያ

ግንቦት 12/2014 ዓ/ም

ሐዋሳ

Share this Post